ጎብኝዎች ሊከተሏቸው የሚገቡ ህጎች

1. ጎብኚዎች በቅድሚያ ወደ ፓርኩ ለጉብኝት ሲመጡ ይዘው መቅረብ የሚገባቸው ዶክመንቶች እና ህግጋት።

-    ማንኛውም ጎብኚ ወቅታዊ ዜግነቱን/ማንነቱን ማሳየት የሚችል የታደሰ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፤ መንጃ ፈቃድ፤ ፓስፖርት ወዘተ...) አንዱን ይዞ መገኘት አለበት፡፡
-    የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ያላቸው ጎብኚዎች የመግቢያ ክፍያ እንደ ኢትዮጵያዊ የሚከፍሉ ሲሆን፤ ይህንን ጥቅም ለማግኘት የታደሰ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
-    በኢትዮጵያ የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ ይዘው የሚመጡ የውጭ ሀገር ዜጎች የመግቢያ ክፍያን የሚከፍሉት እንደ ውጭ ሀገር ዜጋ ነው፡፡

2. ወደ ፓርኩ ይዞ መግባት የተከለከሉ ወይም የማይገቡና የማይፈቀዱ:: ወደ ፓርክ ለማስገባት ከተከለከሉት መሀል ከዚህ በታች ያሉት ይጠቀሱ፡፡

-  ማንኛውም ዓይነት የጦር መሳሪያዎችና የጦር መሳሪያ አካላት፤
-  ስለታማ ነገሮች፤
-  ማንኛውም ዓይነት ኬሚካልና ንጥረ ነገሮች፤
-  ከህጻናት ምግብ በስተቀር ማንኛውም ዓይነት ምግብና መጠጥ፤
-  ፓወር ባንክ፤ ዋይፋይ ራውተር፤ ፍላሽ ዲስክና ሀርድ ዲስክ፤
-  መድሃኒቶች፤
-  ማንኛውም አደንዛዥ እጽ (እጽ፣ ሲጋራ፣ ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ፣ ጫት፣ አልኮል እና የመሳሰሉት)
-  ቴፕ መቅጃ፤
-  የግል ካሜራዎችና የካሜራ ድሮን፤
-  ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (ላፕቶፕ፣ ኪቦርድ፣ ስፒከሮች እና የመሳሰሉት)
-  ማንኛውም ፈሳሽ ነገሮች (ጄል፣ ስሞቲክስ እና የመሳሰሉት)
-  ለአገልግሎቱ ክፍያ ካልፈጸሙ በቀር የሙሽራ፣ የልደት፣ የምርቃት እና ሌሎች ኩነቶች አልባሳት
-  የቤት እንስሳት ወዘተ …

3. በፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት።

-  በጉብኝት ወቅት ሳርም ሆነ ለዉበት የተቀመጡ ነጫጭ ድንጋዮች መርገጥ የተከለከለ ነው።
-  አበባ፣ ቅጠል እና የዛፍ ቅርንጫፍ መቁረጥ የተከለከለ ነው፡፡
-  የተጠቀሙበትን ማንኛዉም ቆሻሻ ለዚህ ጥቅም እንዲዉሉ ተደርገዉ በየቦታዉ በተዘጋጁ ቅርጫቶች እንዲጥሉ እናሳስባለን፡፡
-  በጉብኝትዎ ወቅት የሚያገኟቸዉን ቅርሶች፣ የዐዉደ ርዕይ ክፍል ግድግዳዎች፣ መስታወቶች፣ ቪዲዮ ማሳያ ስክሪኖች እና ሌሎች የመረጃ መስጫዎችን መንካትም ሆነ መደገፍ የተከለከለ ነው፡፡
-  ያለአግባብ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራትም ሆነ መጮህ እንዲሁም በመሮጥ ሌሎች ጎብኚዎችን መረበሽ የተከለከለ ነው፡፡
-  የግል ፎቶና ቪዲዮ በመነሳት/በመቀረጽ ምክንያት ጎብኚዎችንና የጉብኝት ስርዓትን መረበሽና ማደናቀፍ የተከለከለ ነው፡፡
-  ህፃናትን ይዘው ወደ ፓርኩ በሚመጡበት ወቅት ህፃናቱን ለብቻቸው መተው የተከለከለ ነው፡፡
-  እንስሳትን ማስፈራራት እና ማስቆጣት እንዲሁም ቆሻሻ፣ ምግብ እና ሌሎች ነገሮችን በእንስሳቱ መከለያ ውስጥ መጣል የተከለከለ ነው፡፡
-  በፓርኩ ውስጥ ማንኛውም አይነት አደንዛዥ እፅ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
-  ጉብኝት ፈጽመው ከፓርኩ እስኪወጡ ድረስ የጎብኚ መለያ የእጅ ምልክትን ከእጅ መበጠስና መጣል የተከለከለ ነው፡፡
-  በፓርኩ ህግና ደንብ መሰረት ከከፈሉት የጉብኝት/የፎቶግራፍ ጥቅል ውጪ ሌላ አገልግሎት በሚሰጥበት ትኬት መገኘት የተከለከለ ነው፡፡