HOW

BUY TICKETS USING INTERACTIVE SMS

እንዴት?

በስልክ የፅሁፍ መልክት ትኬት መግዛት

Prospective visitors can buy tickets for Unity Park through an interactive SMS payment mechanism available through 6030. This method requires a valid mobile phone number. You can send the specific date and month of your visit in the format DD MM (for example, 05 12 meaning December 5) to 6030 and follow instructions to purchase and receive your tickets through SMS. After receiving your ticket number, you can bring the ticket number to Unity Park, show the ticket number to one of several ticket officers at the gate and enter the park.

ለአንድነት ፓርክ ትኬት ለመግዛት ሲፈልጉ ወደ 6030 የመልዕክት መቀበያ ቁጥር የሚገቡበትን ቀንና ወር በፅሁፍ በመላክ ትኬት መግዛት ይችላሉ። ቀኑን በአዉሮጳውያን አቆጣጠር፣ ቀን እና ወር አድርገው በመላክ (ለምሳሌ፡- ዲሴምበር 5 የጉብኝቱ ቀን ቢሆን ዲሴምበር 12ኛው ወር ስለሆነ፡- 05 12 ብሎ በመላክ) ትኬቱን ለመግዛት የሚጠየቁ መመሪያዎችን በመከተል ትኬቱን በስልክዎ መግዛት ይችላሉ፡፡ በዚህ መልኩ ትኬትዎን ካገኙ በኋላ በፓርኩ በር የቲኬት ቁጥሮን ይዘው በመምጣትና ትኬትዎን በር ላይ ለሚገኙ የቲኬት ባለሙያዎች በማሳየት መግባት ይችላሉ፡፡

TICKET PURCHASE ONLINE THROUGH PHONE CREDIT

በደዕረ ገፅ

Prospective visitors can purchase a ticket through the website (unitypark.et). This method requires a valid mobile phone number; you can purchase a ticket by entering your phone number, verifying it and entering the relevant information. After the information has been entered and you agree to the payable amount, the balance on your phone number will be deducted and a ticket issued. After receiving your ticket number, you can bring your phones to Unity Park, show the ticket to one of several ticket officers at the gate and enter the park.

ለአንድነት ፓርክ ትኬት ለመግዛት ሲፈልጉ ወደ ፓርኩ ድረ ገፅ ማለትም ወደ unitypark.et በማምራት በገፁ የተቀመጡትን መመሪያዎች በመከተል የቲኬት ቁጥር በስልክዎ ማግኘት ይችላሉ። በዚህ መልኩ ትኬትዎን ካገኙ በኋላ በፓርኩ መግቢያ በር የቲኬት ቁጥሮን ይዘው በመምጣትና ትኬትዎን መግቢያ ላይ ለሚገኙ የቲኬት ባለሙያዎች በማሳየት መግባት ይችላሉ፡፡

USING INTERNATIONAL PAYMENT CARDS

ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን በመጠቀም ትኬት መግዛት

Visitors can purchase tickets from the park's website, unitypark.et, using international payment cards. Once you have entered the required personal and payment information on the website, you will receive a ticket number. After receiving the ticket number, you can bring your phone to Unity Park, show the ticket to one of several ticket officers at the gate and enter the park.

ጎብኚዎች ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን በመጠቀም ከፓርኩ ድረ ገፅ ማለትም unitypark.et የመግቢያ ቲኬት መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ በድህረ ገፁ ላይ ተፈላጊ የግል እና የክፍያ መረጃዎችን ካስገቡ በኋላ የሚላክሎትን የትኬት ቁጥር ወደ ፓርካችን ይዘው በመምጣትና ትኬትዎን መግቢያ ላይ ለሚገኙ የቲኬት ባለሙያዎች በማሳየት መግባት ይችላሉ፡፡

Open Hours

ፓርኩ ክፍት የሚሆንበት ሰዓት

Every Tuesday to Sunday from 9:00 - 16:00

ዘወትር ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከጠዋት፡ 3:00 - 10:00

FEES

TICKET PRICING

ክፍያዎች

የትኬት ዋጋዎች

Visitors holding Foreigner passport can only pay in dollars!Visitors holding Ethiopian Origin ID Card will be treated as an Ethiopian
TICKET TYPE ETHIOPIANS (Price in ETB) FOREIGNERS (Price in USD)
REGULAR 300 20
SPECIAL 1,100 50
Unity Park to launch additional tour programs.
It has been more than a year since Unity Park was officially inaugurated. In response to repeated questions and suggestions from visitors, our park is now offering a variety of new tour services starting from Saturday, January 16/2021. These new services allow visitors to visit the park during night time on selected days and also create an opportunity for a wedding and birthday photography program.
 • Family Evening: To visit the park on Thursdays, Saturdays and Sundays from 5 pm to 9 pm.
  • Entrance fee per person – 1000 birr for Ethiopians and 50$ for foreigners.
 • Wedding Photo Program: A wedding photography program, throughout the week except Mondays, including holidays.
  • Entrance fee per person – 1000 birr for Ethiopians and 50$ for foreigners.
 • Birthday Photo Program: birthday photography program, throughout the week except Monday, including holidays.
  • Entrance fee per person – 1000 birr for Ethiopians and 50$ for foreigners
Note: The park's previous regular and special ticket tour services will continue as usual from Tuesday to Sunday from 3:00 am - 5:00 pm and the entrance fee for regular ticket is 300 Birr (for Ethiopians) or $ 20 (for foreigners) and Special ticket is 1100 birr (for Ethiopians) or $ 50 (for foreigners). Terms of service
 • Visitors of the Family evening, Wedding and Birthday Photography program can use food and drink from cafes and restaurants in our park; bringing in food and drink is prohibited.
 • All payments must be made in advance by the bank; You can use our Commercial Bank of Ethiopia account 1000294128388 or 6030 or our USD account 1000314918798.
 • Every visitor must have with them a valid identification document.
 • Every visitor must register at least 24 hours in advance.
 • Payment made for the usual tour packages (regular and special tickets) will not be applicable for the above-mentioned tour services.

For further information please visits our website https://unitypark.et or call +251118578718.

የውጭ ዜጎች ክፍያ በዶላር ብቻ ነው መክፈል የሚችሉትየትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ የያዙ የውጭ ሃገር ዜጎች እንደ ኢትዮጵያዊ ይስተናገዳሉ
የትኬት አይነት ለኢትዮጵያዊያን(ዋጋ በብር) ለውጪ ዜጋ(ዋጋ በዶላር)
መደበኛ 300 20
ልዩ 1,100 50
የአንድነት ፓርክ አዳዲስ የጉብኝት ፕሮግራሞችን ሊጀምር ነው፡፡
የአንድነት ፓርክ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ከጎብኚዎች በተሰጡን ተደጋጋሚ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች መሰረት ፓርካችን የተለያዩ አዳዲስ የጉብኝት አገልግሎቶችን ከመጪው ቅዳሜ ጥር 8/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለጎብኚዎቻችን አቅርቧል፡፡ እነዚህ አዳዲስ አገልግሎቶች ጎብኚዎች ፓርኩን በተመረጡ ቀናት በምሽት እንዲጎበኙ፤ የጋብቻ እና የልደት ፎቶግራፍ ፕሮግራም እንዲያካሂዱ እድል የሚፈጥሩ ናቸው፡፡
 • የቤተሰብ ምሽት፡ ሐሙስ፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከምሽቱ 11፡00 እስከ 3፡00 ሰዓት ፓርኩን ለመጎብኘት የሚያስችል ነው፡፡
  • የመግቢያ ዋጋ ለአንድ ግለሰብ፡- ለኢትዮጵያዊያን 1000 ብር ለውጭ ሃገር ዜጎች 50$፡፡
 • የሙሽሮች ፎቶ ፕሮግራም፡ ከሰኞ በስተቀር ሳምንቱን በሙሉ በዓላትን ጨምሮ የጋብቻ ፎቶግራፍ ፕሮግራም ማካሄድ የሚያስችል ነው፡፡
  • የመግቢያ ዋጋ ለአንድ ግለሰብ፡- ለኢትዮጵያዊያን 1000 ብር ለውጭ ሃገራት ዜጎች 50$
 • የልደት ፎቶ ፕሮግራም- ከሰኞ በስተቀር ሳምንቱን በሙሉ በዓላትን ጨምሮ የልደት ፎቶግራፍ ፕሮግራም ማካሄድ የሚያስችል ነው፡፡
  • የመግቢያ ዋጋ ለአንድ ግለሰብ፡- ለኢትዮጵያዊያን 1000 ብር ለውጭ ሃገራት ዜጎች 50$
ማሳሰቢያ: ፓርኩ ከዚህ በፊት የሚሰጣቸው የመደበኛ እና ልዩ ቲኬት የጉብኝት አገልግሎቶች ዘወትር ከማክሰኞ እስከ እሁድ ከጠዋቱ 3:00 - 11:00 ሰዓት የሚቀጥሉ ሲሆን የመግቢያ ዋጋው ለመደበኛ ትኬት 300 ብር (ለኢትዮጵያውያን) ወይም 20 ዶላር (ለውጭ ዜጎች) ሲሆን፤ ልዩ ትኬት 1100 ብር (ለኢትዮጵያውያን) ወይም 50 ዶላር (ለውጭ ዜጎች) ነው ፡፡ የአገልግሎት ደንቦች
 • ለቤተሰብ ምሽት፣ ለጋብቻ እና የልደት ፎቶግራፍ ፕሮግራም የሚመጡ ጎብኚዎች ምግብ እና መጠጥ መጠቀም ከፈለጉ በፓርካችን ከሚገኙ ካፌ እና ሬስቶራንቶች መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ ምግብም ሆነ መጠጥ ከውጭ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
 • ሁሉም ክፍያዎች በቅድሚያ በባንክ መከፈል ይኖርባቸዋል፤ ለዚህም የፓርካችንን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 1000294128388 ወይም 6030 መጠቀም ይቻላል፡፡
 • ማንኛውም ጎብኚ አገልግሎቱን ለማግኘት ሲመጣ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ ይዞ መገኘት ይኖርበታል፡፡
 • አገልግሎቶቹን ለማግኘት ከፕሮግራሙ ቢያንስ 24 ሰዓታት ቀደም ብሎ ማስመዝገብ ያስፈለጋል፡፡
 • ለሌሎች አገልግሎቶች (ለመደበኛ እና ልዩ ቲኬት) በተከፈለ ክፍያ ከላይ የተጠቀሱትን አዳዲስ የጉብኝት አገልግሎቶች ማግኘት አይቻልም፡፡

ለተጨማሪ መረጃ እባክዎ ድረገፃችንን https://unitypark.et ይጎብኙ ወይም በፓርካችን የመረጃ ስልክ ቁጥር +251118578718 ይደውሉ።

SPECIAL PACKAGE

ልዩ የሚሰጡ አገልግሎቶች

Special ticket holders are allowed to visit the inside of Menilik's palace complex including the Emperor's bedroom, reception room, prayer room, Etege Taytu's bedroom, the prince's bedroom, the small banquet room and the war minister's waiting room. Special ticket holders will have a tour guide that will accompany them throughout the tour. In case there is a queue, priority will be given for Special ticket holders.

ክቡራት ደንበኞቻችን በልዩ ትኬት እና መደበኛ ትኬት መካከል ያሉ ልዩነቶች፦
ልዩ ትኬት የያዘ ሰው በመደበኛ ትኬት ከሚጎበኟቸው ቦታዎች በተጨማሪ
1. የዐፄ ምኒልክን እልፍኞችን ይጎበኛል ማለትም የዐፄ ምኒልክ መኝታ ክፍል፣ ፀሎት ቤት፣ ፅህፈት ቤት፣ የልዑላን ማረፍያ፣ የእቴጌ ጣይቱ መኝታ ክፍል፣ የጦር ሚንስትሩን ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ማረፊያ ክፍል ይጎበኛሉ፤
2. አስጎብኚ በተለያየ ቋንቋ (አማርኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ እንግሊዘኛ እና አረብኛ) ይመደብልዎታል፤
3. ወረፋ በሚኖርበት ጊዜም ቅድሚያ ይሰጦታል።

VARIOUS SERVICES INSIDE THE PARK

የተለያዩ የፓርክ ዉስጥ ግብይቶች

All purchases inside the park, including but not limited to souvenirs, food and beverages are done in cash or via ATM cards. For visitor’s who want to exchange their cash into the local currency, forex enabled ATMs are readily available.

ማንኛዉም በግቢ ውስጥ የሚካሄድ የቁሳቁስ ግዢ እና የአገልግሎት ክፍያዎች በጥሬ ገንዘብ እና በኤ.ቲ.ኤም ካርድ ማከናወን እንደሚችሉ ለመግለፅ እንወዳለን። በዉጭ ሃገር ገንዘቦች ግብይት መፈፀም ለሚፈልጉ ጎብኚዎች የዉጭ ምንዛሬ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች ዝግጁ ናቸው።