ማሳሰቢያ
ጎብኚዎች ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ይዞ መገኘት ሲኖርባቸው በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅድመሁኔታዎች
ካላሟሉ ፓርኩን መጎብኘት አይችሉም።
የሚከለከል
ጎብኚዎች ይዘው መምጣት የሌለባቸው ነገሮች።
- - ስለት
- - ተቀጣጣይ ቁሶች
- - የጦር መሳሪያዎች
- - ምግብ መጠጦች እና ጣፋጭ ነገሮች
- - ማስቲካ
- - የመዋቢያ ቁሶች
- - የግል ካሜራዎች
- - ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች
- - ሲጋራ እና አደንዛዥ ዕጾች
- - አደንዛዥ ዕፆች
- - የቤት እንስሳት
ስነምግባር
በፓርኩ ውስጥ ማድረግ የተከለከሉ ተግባራትና ባህሪያት።
- - በጉብኝት ወቅት ሳርም ሆነ ለዉበት የተቀመጡ ነጫጭ ድንጋዮች መርገጥ፡፡
- - የተጠቀሙበትን ማንኛዉም ቆሻሻ ባልተፈቀዱ ቦታዎች መጣል፡፡ ለዚህ ጥቅም እንዲዉሉ ተደርገዉ በየቦታዉ የተዘጋጁትን ቅርጫቶች እንዲጠቀሙ እናሳስባለን፡፡
- - በጉብኝትዎ ወቅት የሚያገኟቸዉን ቅርሶች እንዲሁም የዐዉደ ርዕይ ክፍል ግድግዶች፣ መስታወቶች እና የቪዲዮ ማሳያ ስክሪኖች፣ የመረጃ ማሳያዎች መንካትም ሆነ መደገፍ፡፡
- - ያለአግባብ ድምፅን ከፍ አድርጎ ማውራትም ሆነ መጮህ እንዲሁም በመሮጥ ሌሎች ጎብኚዎችን መረበሽ፡፡
- - ህፃናትን ይዘው ወደ ፓርኩ በሚመጡበት ወቅት ህፃናቱን ለብቻቸው መተው፡፡
- - እንስሳትን ማስፈራራት እና ማስቆጣት፡፡
- - ቆሻሻ፣ ምግብ እና ሌሎች ነገሮችን በእንስሳቱ መከለያ ውስጥ መጣል፡፡
- - በፓርኩ ውስጥ ማንኛውም አይነት አደንዛዥ እፅ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡